ደም ብዛት (Hypertension) ደም ብዛት የምንለው የደም ግፊት መጨመርን ነው

Slides:



Advertisements
Podobné prezentácie
VEĽKÁ BRITÁNIA.
Advertisements

Tvorba a správa Azure VM s následnou optimalizáciou
7., 8. Signalizácia realizovaná LED - diódou
My favorite places in Slovakia
Reforma zdravotníctva na Slovensku
Základné pojmy spojené s BIOS
Naltrexón/Bupropión Okrúhly stôl
Reforma zdravotníctva na Slovensku
Projekt podpora kardiovaskulárneho zdravia v prostredí základných škôl mestskej časti Bratislava - Petržalka.
eu tancujPD.eu tau tancujPD.eu
Prepis prezentácie:

ደም ብዛት (Hypertension) ደም ብዛት የምንለው የደም ግፊት መጨመርን ነው የደም ግፊት ደም በደም ቧንበዎች ውስጥ ለመንቀሳቀስ የሚጠቀመው ሃይል ነው ግፊቱ ከፍ ባለ ቁጥር ልብ ደምን ለማሰራጨት ብዙ መስራት ይኖርበታል የላይኛው የደም ግፊት > 140mmHg የታችኛው የደም ግፊት > 90mmHg Dr.K.D.Begashaw 2014

ልብ Dr.K.D.Begashaw 2014

ልብ የልብ ስራ ደምን ወደ ሰውነት መርጨት ነው ልብ አራት ክፍሎች አሉት የላይኛዎቹ ደም መላሽ (atrium) ሲባሉ የታችኞቹ ደግሞ (ventricle) ከርሰ ልብ በመባል ይታወቃሉ በያንዳንዱ ልብ ምት የቀኝ ከርሰ ልብ መጠኑ እኩል የሆነ ደም ወደ ሳምባ ይልካል፣ የግራው ከርሰ ልብ ደም ወደ ሰውነት ይረጫል Dr.K.D.Begashaw 2014

ልብ Cardiac output: ልብ በአንድ ግዜ ከቀኙ ወይም ከግራው ከርሰ ልብ የሚረጨው የደም መጠን ነው Afterload: ልብ ከግራ ከርሰልብ ወደ ሰውነት ለማሰራጨት የሚጠቀመው ሃይል ሲሆን Preload: ደግሞ ልብ ደምን ከመርጨቱ በፊት ያለው የልብ ጡንቻ የመለጠጥ አቅም ነው Dr.K.D.Begashaw 2014

ደም ብዛት ጤነኛ የደም ግፊት 120/80mmHg ነው የደም ግፊት ከ 140/90mmHg ካለፈ ደም ብዛት ይባላል የደም ብዛት በአብዛኛው ምክንያቱ ምን እንደሆነ አይታወቅም የኩላሊት ደም ቧንቧ መጥበብ ደም ብዛት ያስከትላል ጨው የበዛበት ምግብ መመገብ፣ የእርግዝና መከላከያ እንክብሎች ደም ብዛት ሊያስከትሉ ይችላሉ Dr.K.D.Begashaw 2014

በእርግዝና ግዜ የሚያጋጥም ደም ብዛት ከ22 የእርግዝና ሳምንት በፊት የሚያጋጥም (pre existente hypertensie) ይህ አይነቱ የደም ብዛት የእርግዝናው ግዜ ሲጨምር አብሮ ከፍ ይላል ይህ ደም ብዛት ከወለዱ ከ6 ሳምንት በሁዋላም ከቀጠለa ቀድሞም የነበረ ነበር ማለት ነው (> 140/90mmhg) የእርግዝና ግዜ ደም ብዛት ለእናቱና ለሚወለደው ሕጻን የጤና ችግሮችን ያስከትላል ደም ብዛትk በሽንት ፕሮቲን ከማስወገድ ጋር ካጋጠመ እርጉዟ ወደ ማህጸን ሐኪም ልትላክ ይገባል (pre-eclampsie) Dr.K.D.Begashaw 2014

ደም ብዛት ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ደም ብዛትን ሊያስከትሉ ወይም ሊያባብሱ ይችላሉ ውፍረት፣አልኮል፣ ሲጋራ ማጤስ ስኳር በሽታ ያለመንቀሳቀስ የካልሲየም፣ፖታሲየም፣ማግኔዚየም እጥረት ብስጭት፣ እርጅና Dr.K.D.Begashaw 2014

ደም ብዛት እድሜ እየጨመረ ሲመጣ የደም ብዛት የማጋጠም እድልም ከፍ ይላል ምት (stroke (CVA))በደም ብዛት ምክንያት ከሚያጋጥሙ በሽታዎች አንዱ ነው ከ 40-59ዓመት ወንዶች የላይኛው የደም ግፊታቸው ከ 160-180mmHg ከሆነ ጤነኛ የደም ግፊት ካላቸው ወንዶች በአራት እጥፍ ምት ያጋጥማቸዋል ደም ብዛት ልብ ድካምንና የልብ ጡንቻ መሞትን (heart attack) ያስከትላል Dr.K.D.Begashaw 2014

ደም ብዛት ማጨስና የስባት (ኮሌስቴሮል) መብዛት ከደም ብዛት ጋር ካጋጠሙ የምትና የልብ በሽታ እድል በጣም ከፍ ይላል አልኮል የደም ግፊት ከፍ እንዲል ያደርጋል Dr.K.D.Begashaw 2014