Prezentácia sa nahráva. Prosím počkajte

Prezentácia sa nahráva. Prosím počkajte

ደም ብዛት (Hypertension) ደም ብዛት የምንለው የደም ግፊት መጨመርን ነው

Podobné prezentácie


Prezentácia na tému: "ደም ብዛት (Hypertension) ደም ብዛት የምንለው የደም ግፊት መጨመርን ነው"— Prepis prezentácie:

1 ደም ብዛት (Hypertension) ደም ብዛት የምንለው የደም ግፊት መጨመርን ነው
የደም ግፊት ደም በደም ቧንበዎች ውስጥ ለመንቀሳቀስ የሚጠቀመው ሃይል ነው ግፊቱ ከፍ ባለ ቁጥር ልብ ደምን ለማሰራጨት ብዙ መስራት ይኖርበታል የላይኛው የደም ግፊት > 140mmHg የታችኛው የደም ግፊት > 90mmHg Dr.K.D.Begashaw 2014

2 ልብ Dr.K.D.Begashaw 2014

3 ልብ የልብ ስራ ደምን ወደ ሰውነት መርጨት ነው
ልብ አራት ክፍሎች አሉት የላይኛዎቹ ደም መላሽ (atrium) ሲባሉ የታችኞቹ ደግሞ (ventricle) ከርሰ ልብ በመባል ይታወቃሉ በያንዳንዱ ልብ ምት የቀኝ ከርሰ ልብ መጠኑ እኩል የሆነ ደም ወደ ሳምባ ይልካል፣ የግራው ከርሰ ልብ ደም ወደ ሰውነት ይረጫል Dr.K.D.Begashaw 2014

4 ልብ Cardiac output: ልብ በአንድ ግዜ ከቀኙ ወይም ከግራው ከርሰ ልብ የሚረጨው የደም መጠን ነው
Afterload: ልብ ከግራ ከርሰልብ ወደ ሰውነት ለማሰራጨት የሚጠቀመው ሃይል ሲሆን Preload: ደግሞ ልብ ደምን ከመርጨቱ በፊት ያለው የልብ ጡንቻ የመለጠጥ አቅም ነው Dr.K.D.Begashaw 2014

5 ደም ብዛት ጤነኛ የደም ግፊት 120/80mmHg ነው የደም ግፊት ከ 140/90mmHg ካለፈ ደም ብዛት ይባላል
የደም ብዛት በአብዛኛው ምክንያቱ ምን እንደሆነ አይታወቅም የኩላሊት ደም ቧንቧ መጥበብ ደም ብዛት ያስከትላል ጨው የበዛበት ምግብ መመገብ፣ የእርግዝና መከላከያ እንክብሎች ደም ብዛት ሊያስከትሉ ይችላሉ Dr.K.D.Begashaw 2014

6 በእርግዝና ግዜ የሚያጋጥም ደም ብዛት ከ22 የእርግዝና ሳምንት በፊት የሚያጋጥም (pre existente hypertensie) ይህ አይነቱ የደም ብዛት የእርግዝናው ግዜ ሲጨምር አብሮ ከፍ ይላል ይህ ደም ብዛት ከወለዱ ከ6 ሳምንት በሁዋላም ከቀጠለa ቀድሞም የነበረ ነበር ማለት ነው (> 140/90mmhg) የእርግዝና ግዜ ደም ብዛት ለእናቱና ለሚወለደው ሕጻን የጤና ችግሮችን ያስከትላል ደም ብዛትk በሽንት ፕሮቲን ከማስወገድ ጋር ካጋጠመ እርጉዟ ወደ ማህጸን ሐኪም ልትላክ ይገባል (pre-eclampsie) Dr.K.D.Begashaw 2014

7 ደም ብዛት ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ደም ብዛትን ሊያስከትሉ ወይም ሊያባብሱ ይችላሉ
ውፍረት፣አልኮል፣ ሲጋራ ማጤስ ስኳር በሽታ ያለመንቀሳቀስ የካልሲየም፣ፖታሲየም፣ማግኔዚየም እጥረት ብስጭት፣ እርጅና Dr.K.D.Begashaw 2014

8 ደም ብዛት እድሜ እየጨመረ ሲመጣ የደም ብዛት የማጋጠም እድልም ከፍ ይላል
ምት (stroke (CVA))በደም ብዛት ምክንያት ከሚያጋጥሙ በሽታዎች አንዱ ነው ከ 40-59ዓመት ወንዶች የላይኛው የደም ግፊታቸው ከ mmHg ከሆነ ጤነኛ የደም ግፊት ካላቸው ወንዶች በአራት እጥፍ ምት ያጋጥማቸዋል ደም ብዛት ልብ ድካምንና የልብ ጡንቻ መሞትን (heart attack) ያስከትላል Dr.K.D.Begashaw 2014

9 ደም ብዛት ማጨስና የስባት (ኮሌስቴሮል) መብዛት ከደም ብዛት ጋር ካጋጠሙ የምትና የልብ በሽታ እድል በጣም ከፍ ይላል አልኮል የደም ግፊት ከፍ እንዲል ያደርጋል Dr.K.D.Begashaw 2014


Stiahnuť ppt "ደም ብዛት (Hypertension) ደም ብዛት የምንለው የደም ግፊት መጨመርን ነው"

Podobné prezentácie


Reklamy od Google